የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ የበላይ አመራሮች ከኢኢግልድ አመራሮች ጋር ውይይትና የስራ ጉብኝት አካሄዱ

በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ምክትል ዋና ስራ አስፈጻሚ ወ/ሪት መለከት ሰሀሉ የተመራ የተቋሙ የበላይ አመራሮች ቡድን የኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ግብዓቶች ልማት ድርጅት በቅርቡ በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ስር እንዲካተት መደረጉን መሰረት በማድረግ የኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ግብዓቶች ልማት ድርጅት የበላይ አመራሮች ጋር ታህሳስ 16 ቀን 2017 ዓ.ም የትውውቅ እና የሥራ ጉብኝት አካሄዱ፡፡

በዕለቱ የኢኢግልድ ዋና ስራ አስፈጻሚ ወ/ሮ የሺመቤት ነጋሽ የድርጅቱን አጠቃላይ ሁኔታ የሚገልጽ አጭር ሪፖርት ያቀረቡ ሲሆን ከኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ግሩፕ አመራሮችም ሪፖርቱን መነሻ በማድረግ ማብራሪያ በሚያስፈልጋቸው ጉዳዮች ላይ ጥያቄዎች ቀርበው ምላሽ ተሰጥቷል፡፡

የበላይ አመራሮች የቀረበውን ሪፖርት መነሻ በማድረግ አስተያየቶችን የሰጡ ሲሆን በመጨረሻም የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ምክትል ዋና ስራ አስፈጻሚ በድርጅቱ ነባራዊ ሁኔታ እና በቀጣይ በሚኖረው የግንኙነት ላይ አስተያየቶችን በመስጠት ውይይቱ ተጠናቋል፡፡

በመጨረሻም ቡድኑ በዋና መሥሪያ ቤት የሚገኙ የስራ ክፍሎችን ጉብኝት አካሂደዋል፡፡

የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ በቅርቡ በስሩ ካካተታቸው 8 አዳዲስ ቁልፍ ተቋማት መካከል የኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ግብዓቶች ልማት ድርጅት አንዱ መሆኑ ይታወቃል፡፡